Partly Cloudy Partly Cloudy Sunny
18C 26C 25C
ክስኞ ሮብ

ሃገር ፍቅር ቲያትር

የሀገር ፍቅር ቴአትር በአዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም ጭምር አንጋፋ ትያትር ቤት ነው፡፡ከ74 ዓመታት በላይ የባህል መድረክ ሆኖ የቆየ ሲሆን ዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃና ድራማ የተወለደበት ያደገበት ታሪካዊ ትያትርም ነው፡፡ብዛት ያላቸው እንደ ጥላሁን ገሠሠ፣አስቴር አወቀ እና ፍሬው ሀይሉ የመሳሰሉ ታዋቂ ድምፃውያን የዘፋኝነት ሀሁን የጀመሩት ሀገር ፍቅር ትያትር መድረክ ላይ ነው፡፡ባለፉት አስር ዓመታት የሀገር በቀልም ሆኑ የአውሮፓ ፀሐፊ ተውኔቶች ዊሊያም ሼክስፒር፣ፈሪድሽ ሺለር፣ሄንሪክ ኢብሰን እና ሞሊየር ስራዎች ተዘጋጅተው በሀገር ፍቅር ትያትር ቀርበዋል፡፡

የሀገር ፍቅር ትያትር ቤት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የጣሊያንን ወረራ ለመቋቋም የሀገር ፍቅር ማህበርን በመሰረቱበት በ1927 ዓ.ም የተቋቋመ ነው፡፡የመስራቾቹ ፍላጎት የነበረው የኢትዬጵያን ህዝብ ከዳር እስከዳር ለማነሳሳትና የአርበኝነት አይበገሬነታቸውን ለመቀስቀስ ነበር፡፡የመጀመሪያው ተውኔት የቀረበው ከአዳራሽ ውጪ መሃል አዲስ አበባ ምኒሊክ አደባባይ ነበር፡፡ምንም እንኳን ጣሊያን ወረራውን ብታካሂድም የሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ግን ወረራውን ለመቋቋም ችሎ ነበር፡፡ይሁን እንጂ ጣሊያን አገር ውስጥ በቆየባቸው ጊዜያት ይህ ነው የማይባሉና ፋሺስታዊ መልክት ያላቸው ተውኔቶች ለእይታ ቀርበውበታል፡፡

ጣሊያን ኢትዮጵያን ለቆ ከወጣ በኋላ በ1934 ዓ.ም የትያትር ቡድን አባላቱ ከምኒሊክ አደባባይ አሁን ወዳለበት ፒያሳ አካባቢ ተዛወሩ፡፡እዚህ ቦታ ላይ የነበረ አንድ አሮጌ የጣሊያን የምሽት ክለብ ታድሶ የትያትር ማሳያ አዳራሽ ሆነ፡፡በ1948 ዓ.ም ለ25ኛው የአፄ ኃይለስላሴ ዘመን የሀገር ፍቅር ትያትርን አዲስ አበባ ውስጥ አስሩ ከዚያም የሀገር ፍቅር ትያትር የብዙሃኑ ትያትር ብሔራዊ ትያትር ደግሞ በአብዛኛው በከፍተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል ትያትር ቤት ሆነ፡፡

የሀገር ፍቅር ትያትር በመደበኛነት ከሚቀርባቸው ትያትሮች በተጨማሪ ከመድረክ በቀጥታ በኢትዮጲያ ሬዲዮ የሚተላለፍ ፕሮግራሞችን ያቀርብ ነበር፡፡በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ውጪ ያለው ህብረተሰብ የሀገር ፍቅርን ዝግጅቶችን መመልከት እንዲችል በየቦታው ዝግጅቶቹን ይዞ በመጓዝ ትዕይንቶችን ለታዳሚዎች አቅርቧል፡፡

ከኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት በኋላና በደርግ ዘመነ መንግስት የሀገር ፍቅር ቴአትር ሶሻሊስታዊ መልክት ያላቸው ተውኔቶችንና ትዕይንቶችን ለሕዝብ ማቅረብ ጀመረ፡፡በዚህን ወቅት የሙዚቃ ባለሙያዎቹና ተዋንያኖች በአብዛኛው ቁጥጥር ይካሄድባቸው ነበር፡፡የቴአትር አዘጋጆች ሥራዎች በመንግስት ሳንሱር ይደረግባቸው ነበር፡፡በ1968 ዓ.ም ‹‹ዕቃው››በተሰኘው ቴአትር ምክንያት ደራሲው የሆኑት አቶ ተስፋዬ ገሰሰ ስራውን ለመድረክ በማብቃታቸው ለስር ተዳርገው ነበር፡፡ፀረ-ደርግ እና ፀረ-አብዮት በሚል ሰበብ፡፡

ከደርግ ስርዓት መውደቅ በኋላ በ1983 ዓ.ም የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በአዲስ መልክ ጀመረ፡፡በአሁን ጊዜ ቴአትር ቤቱ 120 በላይ ሠራተኞች ሲኖሩት ከነዚህ ውስጥ 80 የሆኑት ተዋንያኖችና የሙዚቃና የዳንስ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ቴአትር ቤቱ የሳምንት ቀናት ሁሉ የቴአትርና የሙዚቃዊ ድራማ ፕሮግራም የሚቀርብ ሲሆን ፊልም በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የሙዚቃ ዝግጅቶቹን ደግሞ በበዓላት ቀናት ያቀርባል፡፡


የባህልና የቱሪዝም ሀብቶቻችን
በከተማችን ልማት ውስጥ
ግንባር ቀደም ተዋናዮች እንዲሆኑ
እንሰራለን፡፡

         
Developed by JoomVision.com

መረጃዎች እንድንልክልዎ ይመዝገቡ