አዲስ አበባ በመርካቶ እንብርት ለኪነ-ጥበብ ፋይዳ ያዋላችው በሀገሪቷ በጣት ከሚቆጠሩ ብርቅዬ ትያትር ቤቶች መካከል "ራስ ቴአትር"ን ሾማለች የዚህ ብርቅዬ ቴአትር ቤት ታሪካዊ አመጣጥ ምን ይመስላል; ዝርዝር መረጃው እንደሚከተለው ተቀምጧል፡፡
በ193ዐ ዓ.ም. በራስ ቴአትር ተ/ኃይማኖት ስም ተሰይሞ "ሲኒማ ራስ" የተሰኘው ቤት የህንፃ ግንባታው የተጠናቀቀው በ1929 ዓ.ም. መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዛሬው ራስ ቴአትር ሲኒማ ራስ ኃይሉ በመባል ተሰይሞ የተለያዩ ፊልሞችን ማሳየት ጀምሮ ነበር፡፡ በወቅቱ ጣልያኖች ይህንን ስም የሰጡበትም ይሁን በራስ ኃይሉ ስም እንዲሰየም ያደረጉበት ቱባ ቱባ ምክንያቶች ነበራቸው፡፡
ወራሪው የፋሽሽት ኢጣሊያን መንግስት ሲኒማ ቤቱን የሞሶሎኒን አገዛዝ የተሳለጠ ለማድረግ ፋሽስታዊ አመለካከቱንም በህዝቡ ውስጥ ለማስረፅ በማሰብ ለዚህ አለማ አመቺ እና ግብ መቺ የሆኑ ፊልሞችን እያመጣ ሲያሳይ ቆይቷል፡፡ በአንፃሩም የአርበኞች ትግል እንዳይጠናከር ሰፊ መሰረት ያለው የአንድነት ስሜቱንም እንዲሸረሽርና ማዕከላዊነቱ ፈፅሞ እንዲጠፋ ብዙ ጥሯል፡፡
ሲኒማ ቤቱ የህብረተሰቡን የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊና መሰል ፋይዳ ያላቸው መገለጫዎቹን ወደ ጐን በመተው በመረጠው የአስተሳሰብ ጐዳና ጥቂት ፊልሞችን ሲያሳይ ቆይቷል፡፡ ይህንንም ስውር አላማውን ዳር ለማደረስ ሲኒማ ቤቱን ህዝቡ የራሱ ብሎ እንደተቀበለውና "ላሜ ሆይ ሳሩን አይተሽ ገደሉን ሳታይ" እንዲል የሀገራችን ወግ ሲኒማ ቤቱን ከወራሪው መንግስት የራቀና የራሱ የህብረተሰቡ ለማስመሰል በራስ ኃይሉ ስም ሳይሞት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡
በ1933ዓ.ም. ፋሺስት የኢጣልያ መንግስት ከመላው አገር ከወጣ በኋላ ሲኒማ ቤቱ ጥቂት ሲሰራ ቢቆይም የኋላኋላ አገልግሎቱን በማቋረጥ ከ1948 ዓ.ም. ጀምሮ በግሪካዊው አስመጪ እና ላኪ ሚስተር ጆርጅ ሜሪሊያስ ባለቤትነት የቡናና የቦሎቄ ማበጠሪያ ወፍጮ ቤትም ሆኖ ሲሰራ ቆይቶ በ1959 ዓ.ም. ደግሞ የመዘጋት እጣ ገጥሞታል፡
በ1952 ዓ.ም. አርመናዊ ዜግነት ያላቸው ሰው የሲኒማውን ስራ ሲያስቀጥሉት ቆይተው በ1955 ዓ.ም. ደግሞ የመዘጋት እጣው ተደገመ፡ ድፍን ሦስት አመታት ደግሞ ለቢሊያርድ ማጫወቻነት፣ ለመጋዘንነትና ለሌላም አገልግሎት ሲውል ቆይቶ በ1958 ዓ.ም. በሮበርት ጄሪያን/ አርመናዊ ናቸው/ እሳቸው እጅ ገብቶ እስከ 1968 ዓ.ም. የሲኒማ ቤትነቱን ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
በ1968 ዓ.ም. የከተማ ትርፍ ቤቶችን እና ቦታዎች ለመንግስት ባደረገው አዋጅ ሲኒማ ቤቱ በባህልና ሲፖርት ጉዳይ ሚኒስቴር ሥር ሆነ፡፡

Addis Ababa Culture and tourism is a division of Addis Ababa City Administration