Partly Cloudy Partly Cloudy Sunny
21C 26C 25C
ክስኞ ሮብ

ዜና


በገቢ ታክስና ግብር አሰባሰብን አስመልክቶ በህብረተሰቡ እየታየ ያለውን የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያግዙ የተለያዩ ኪነጥበብ ስራዎችን ለህዝብ ማድረሱን የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቢሮው ጥር 15/2004 ዓ.ም ላይ በስሩ የሚገኙ 3 ዋና የስራ ሂደቶች 4 ቴአትር ቤቶች ፣ የአዲስ አበባ ቤተ-መጽሐፍት ወመዘክርና የአዲስ አበባ ሙዚየም እንዲሁም የአስሩም ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት የቢሮው የ6 ወር አፈጻጸም ግምገማ ሲካሄድ እንደተገለጸው አገራችን ካስቀመጠችው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሳካት በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት በተደረጉ እንቅስቃሴዎች በህዳሴው ግድብ ላይ የሚያተኩሩ ፣ የሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ እንዲሁም በትምህርት ጥራት ፣ ሽፋንና ፍትሃዊነት ላይ ያተኮሩ ዝማሬዎች ፣ ድራማና ሙዚቃዊ ድራማዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለህዝብ መድረሳቸው ተገልጻDል፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ ገብረፃዲቅ ሀጎስ እንደገለጹት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ ህብረተሰብ እየታየ ያለውን የስራ ባህል እድገት እና የቁጠባ ባህል ጅምር እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም ለከተማችን ዘላቂ እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወተውን የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በኪነ-ጥበብ ለማገዝ ቢሮው እቅድ ነድፎ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውሰው ባለፉት 6 ወራትም የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት በመደገፍና ቢሮው ከቆመለት ሁነኛ ዓላማ አንፃር በከተማዋ የብሔር ብሔረሰቦች ባህል ግንባታ ላይና የቅርሶች አጠባበቅና አያያዝ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን አብራርተዋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ አያይዘውም በመልካም ስነ መግባር የታነፁና ሙስናን የሚፀየፍ ዜጋ ለመፍጠር እንዲያግዝ ከፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለ75 የሴክተሩ 

አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና ከመስጠቱም ባሻገር በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ከፖሊስና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን የህገወጥ ቅጅ እንቅስቃሴን ለመከላከል የሚያስችል ስኬታማ ውይይቶች ተደርገዋል ብለዋል፡፡

በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል አቶ ኩራባቸው ደነቀና ወ/ሮ አዜብ ከበደ የራስ ቴአትርና የህጻናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጆች በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት አመርቂ ተግባራት የተከናወኑ ቢሆንም ከህብረተሰቡ የጥበብ ፍላጎት አንጻር ቴአትር ቤቶቹ በቀጣይ 6 ወራትም የተሻለ ተግባራት ለማከናወን የእቅድ መርሃ ግብር አዘጋጅተው ወደ ተግባር ለመግባት ቅድመ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ6 ወራት የእቅድ ክንውን የከተማዋን መልካም ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደነበረው ተገለጸ፡፡ 

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ.ም በቢሮው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የ6 ወር የእቅድ አፈፃፀም ውይይት ሲካሔድ የቢሮው ኃላፊ አቶ ገ/ፃዲቅ ሀጎስ የመሩት ሲሆን በስሩ ያሉ ተቋማት እና የ10 ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ስራ ሂደቶች ተገኝተዋል፡፡
በቢሮው የጥናት እቅድና በጀት ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል አሰፋ የነበረውን ክንውን ሲያብራሩ ባሳለፍነው 6 ወራት ውስጥ ልማታዊ ባህልን የሚያጎለብቱ እና የቱሪዝም ልማቱን የሚያፋጥኑ በርካታ ቁልፍ ተግባራት መከናወናቸውን ፣ የዘመን መለወጫ የሙዚቃ ዝግጅት በቴአትር ቤቶች ልዩ ልዩ መልእክት ያላቸው ሙዚቃዎች ፣ ድራማዎች ፣ የፓፔት ትርኢቶች  የህጻናትና አዋቂ ቴአትሮች በመድረክ ለህዝብ እንደቀረቡ ፣ በባህልና ቱሪዝም ልማት ላይ የሚያተኩሩ 26 የሬዲዮ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው መተላለፋቸውን ፣ 29 ሺ 30 መጽሄቶች ፣ ብሮሸሮች ፣ የመልካም ዘመን ምኞት መግለጫ ካርዶች መሰራጨታቸውን ፣ 2 የዶክመንተሪ ፊልሞች የከተማዋን መልካም ገጽታ ግንባታና የቱሪስት ፍሰት እንቅስቃሴው ዓይነት መጨመሩ አላማቸው አድርገው እና የአዲስ አበባን 125ኛ ዓመት የልደት በአል አስመልክቶ የከተማዋን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚያስገነዝቡ ዶክመንተሪ ፊልም ተዘጋጅተው ለህዝብ ተሰራጭተዋል፡፡ ለ1 ሺ 276 የባህል እና ቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በህግ እና ደንቡ መሰረት እየሰሩ ሰለመሆኑ ክትትል ተድርጎ 1ሺ 85ቱ በተሰጣቸው ድጋፍ በአሰራራቸው ላይ ማሻሻያ ማድረጋቸውን በተጨማሪም ለ494 ክበባትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቴክኒክ ድጋፍ መደረጉ ፣ የአዲስ አበባ ሙዚየም ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ በመጡ 2 ሺ 875 ሰዎች መጎብኘቱን ፣ የንባብ ባህልን ለማዳበር በመሰራቱ ለ371 ሺ 126 ሰዎች መጽሀፍት ውሰት እና የንባብ አገልግሎት መሰጠቱን ፣ በተለያዩ ህዝባዊ ባዓላት ከማእከል እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ ባለው መዋቅራችን 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን ማሳተፍ 

መቻሉን ለ180 ሺ 415 የከተማዋ ህብረተሰብ ክፍሎች መረጃ እንዲያገኙ መደረጉን ፣ በህገወጥ ቅጂ መብት ጥሰት ላይ በክፍለ ከተሞች አበረታች ክንውኖች የነበሩ መሆኑን እና 8 ጥናቶችን 
ተካሄደው አብዛኞቹ በመድረክ ለህዝብ መቅረባቸውን ፣ ከቴአትር ቤቶች እና ከአዲስ አበባ ሙዚየም የውስጥ ገቢ ብር ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አንድ ሺ አንድ መቶ አስራ አራት ብር ከአስራ ሁለት ሳንቲም      /2.341.114.12/ ከነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ብር ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ሺ ሶስት መቶ ሰላሳ አምስት ብር /291,335/ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱም ተሳታፊዎች ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል የሆቴሎች የደረጃ ምደባ እና ፈቃድ አሰጣጥ ፣ የለውጥ ስራዎች /BPR እና BSC/ ተፈጻሚነት ፣ የሰው ኃይል እጥረት ፣ የተሞክሮ ልውውጥ እና የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት እንደሚገባ ጠቅሰው በጥቅሉ ቢሮው አሁን ያለው አፈጻጸም አበረታች ቢሆንም ባለፈው አፈጻጸም ያጋጠሙ ማነቆዎችንና ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ ከስር ከስር መፍትሔ እየተበጀላቸው በቅንጅት ከተሰራ የመዲናችን አዲስ አበባ መልካም ገጽታ የመገንባት ስራው ከመቼውም ጊዜ የተሸለ ማድረግ እንደሚቻል ከመግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

የህገወጥ ቅጂን ለመከላከልም የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ሰርቷል፡፡

እንደ አቶ ወርቁ መንገሻ የቢሮው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ ገለጻ ቢሮው  በከተማው ውስጥ በባህልና ቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ዘርፍ የተሰማሩት ተቋማት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግና በህግ አግባብ እንዲመሩ በማገዝ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በበጀት ዓመቱ አጋማሽም በከተማዋ ውስጥ ተንሰራፍቶ የቆየውን የህገ ወጥ ቅጅ ለመከላከል የሚያስችል አሰራር ለመዘርጋት የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት በተደረጉ እንቅስቃሴዎች በየካ ፣ አቃቂ ቃሊቲ ፣ ኮልፌ ቀራኒዮና ልደታ ክፍለ ከተማዎች ከ 1 ሺ በላይ በሚደርሱ የኦዲዮቪዢዋል ማህበር ፣ የሙዚቀኞች ማህበር ፣ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት ፣ ከድምፅና ምስል ውጤቶች ሻጭና አከራይ ከፖሊስና ከኃይማኖት ተቋማት ከተወጣጡ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ግንዛቤ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

አቶ አስቻለው ቦጋለ የሙያ ፈቃድና ሬጎላቶሪ ዋና የስራ ሂደት ተወካይ ሲሆኑ በአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ማዕከል ለ125 ተቋማት የሙያ ፈቃድ እድሳትና ለ2 መቶ 33 ተቋማት አዲስ የሙያ ፈቃድ  መሰጠቱን ጠቅሰው በመዋቅሩ ስር በሚገኙ አስሩ ክፍለከተማዎች 1 ሺ 2 መቶ 45 ተቋማት የሙያ ፈቃድ እድሳት እና ለ1 ሺ 1 መቶ ሃያ አንድ አዳዲስ ተቋማት የሙያ ፈቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ ክንውኑ ካለፈው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ጋር ሲነጻጸርም በ 1 ሺ አንድ መቶ ስልሳ አምስት ብልጫ እንዳለው አብራርተዋል፡፡  

Adwa Celebrated የአድዋን ድል 114 ዓመት በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀው ፕሮግራም በአዲስ አበባ ቲያትርና ባህል አዳራሽ የተካሄደ፡፡ በእለቱ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረፃዲቅ ሃጎስ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮና የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮዎች በከተማ አስተዳደር ባሉ የጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ ለመስራት ተፈራረሙ፡፡የሁለቱን ቢሮዎች የጋራ ስምምነቶች የተፈራረሙበት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረፃዲቅ ሃጎስና የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ ናቸው፡፡

Bureau Gave Awardsየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበጀት 2ዐዐ2 ዓ/ም የመጀመሪያው 6 ወር እቅድ አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የሥራ ሂደቶች የክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶች እንዲሁም በ BSC እና BPR ጥናት ላይ ለተሳተፉ ሙያተኞች የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ፡፡
በኪነ ጥበባት ዘርፍ የተንሰራፋውን ህገወጥነት በጋራ መከላከል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኩማ ደመቅሣ አስታወቁ፡፡

ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ይህንን የገለፁት በአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተዘጋጀውንና በከተማዋ ዙሪያ መለስ በሰፈነው የኪነጥበባት ችግሮች ዙሪያ ያተኮረውን የግማሽ ቀን አውደ ጥናት በመሩበት ወቅት ሲሆን፤ የኪነጥበብ ዘርፉ የሚጠበቅበትን እንዳያበረክትና፣ የዘርፉ ባለሙያዎችም ከስራዎቻቸው ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ካደረጋቸዉ ማነቆ ለማላቀቅ ከተናጠል መፍትሄ ይልቅ በጋራ ቅንጅት ተገቢውን ርብርቦሽ ማድረግ ይገባል በሚል ተናግረዋል፡፡

የባህልና የቱሪዝም ሀብቶቻችን
በከተማችን ልማት ውስጥ
ግንባር ቀደም ተዋናዮች እንዲሆኑ
እንሰራለን፡፡

         

መረጃዎች እንድንልክልዎ ይመዝገቡ

የአዲስ አበባ ካርታ