Partly Cloudy Partly Cloudy Sunny
21C 26C 25C
ክስኞ ሮብ

ቱሪዝም

መስህቦች

Tourism በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡- ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦችና ተፈጥሮአዊ የቱሪስት መስህቦች ናቸው፡፡

በቱሪዝም እይታ ተፈጥሮአዊ የቱሪስት መስህቦች የሚባሉት የአየር ሁኔታ፣ የውሃ አካላት /ውቅያኖስ፣ ባህር፣ ወንዞች፣ ፍልውሃዎች፣ እንሰሳትና ዕፅዋት፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የመሣሠሉት ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ የተወሰኑት በመዲናችን ይገኛሉ፡፡

ዝርዝሩን ይመልከቱ...

ቅርሶች

Heritage
አዲስ አበባ ውስጥ በታሪካቸው፣ በስነ ህንፃ ውበታቸው፣ በውስጣቸው በያዟቸው በገንዘብ የማይታመኑ ብርቅና ድንቅ ቅርሶች ታዋቂ የሆኑ አቢያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡ አብያተ ክርስቲናቱ ከከተማዋ ባህል፣ ታሪክና ፖለቲካ ጋር በእጅጉ የተቆራኙ እንደመሆናቸው በከተማችን አሉ ከሚባሉት የቱሪስት መስህቦች ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡

ዝርዝሩን ይመልከቱ...

ታሪክ

History
አፄ ምኒሊክ ከወታደሮቻቸውና ከአማካሪዎቻቸው ጋርሆን አብዛኛውን ጌዜያቸውን ከእምጦጦ ተራራ ቁልቁል በመውረድ ሙቅ የተፈጥሮ ውሃ በሚገኝበት የከተማዋ ክፍለ በመዝናናት ያሳል ነበር፡፡ በኋላም በዚህ ቦታ እጅግ በመማረካቸው የሀገሪቱን መዲና በዚህ አካባቢ አቅራቢያ ሊያዋቅ ችለዋል፡፡ምንም እንኳን ንጉሱ በእንጦጦ የገነቡት መቤታቸው በወቅቱ እጅግ ውብና ማራኪ ቢሆንም አካባቢው በከፍተኛ ቦታ ላይ በመገኘቱ በጣም ቀዝቃዛ ነበር፡፡

ዝርዝሩን ይመልከቱ...

ኮንፍረንስ

ስብሰባዎች እጅግ ሳቢና ከተቀላጠፈ አገልገልት አሰጣጥ ጋር ታላላቅ ብቻ ሳይን አነስተኛ ዎርክሾችና ሴሚናሮች የምታስተናግድ የአህጉራችን መዳረሻ በመሆን ላይ የምትገኝ ከተማ ናት፤፡

የስብሰባ አገልግሎት  አለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል በመሆን ከመላው አለም የሚመጡ ታላላቅ የሀገሪቱ መሪዎች ኣና የተከበሩ እንግዶች የሚያካሂዷቸው አነስተኛ ወርክሾችና ሴሚናሮች የሚያስተናግደው የተባበሩት መንግስታት የስብሰባ ማዕከል  እ.ኤ.አ ከ1958 ጀም የተቀላጠፈ አገልገሎት በመስጠት ስመጥር የሆነ ነው፡፡

ዝርዝሩን ይመልከቱ...

የባህልና የቱሪዝም ሀብቶቻችን
በከተማችን ልማት ውስጥ
ግንባር ቀደም ተዋናዮች እንዲሆኑ
እንሰራለን፡፡

         
Developed by JoomVision.com

መረጃዎች እንድንልክልዎ ይመዝገቡ