አፄ ምኒሊክ ከወታደሮቻቸውና ከአማካሪዎቻቸው ጋርሆን አብዛኛውን ጌዜያቸውን ከእምጦጦ ተራራ ቁልቁል በመውረድ ሙቅ የተፈጥሮ ውሃ በሚገኝበት የከተማዋ ክፍለ በመዝናናት ያሳል ነበር፡፡ በኋላም በዚህ ቦታ እጅግ በመማረካቸው የሀገሪቱን መዲና በዚህ አካባቢ አቅራቢያ ሊያዋቅ ችለዋል፡፡ምንም እንኳን ንጉሱ በእንጦጦ የገነቡት መቤታቸው በወቅቱ እጅግ ውብና ማራኪ ቢሆንም አካባቢው በከፍተኛ ቦታ ላይ በመገኘቱ በጣም ቀዝቃዛ ነበር፡፡በ1986ዓም በክረምት ወቅት ንጉሱና ባለቤታቸው የእንጦጦ ቅዝቃዜ ስለበረታባቸው በፍልውሃ አካባቢ ወደሚገኘው እልፍኛቸው አምርተው ነበር፡፡ታዲያ በወቅቱ ንግስቲቱ በእልፍኛቸው አካባቢ ብዙ ሰው ዳስ ጥሎና ጎጆ ቀልሶ አካባቢውን ሞቅ ያለ መንደር አድርጎት በማየታቸው በጣም ተገረሙ ንጉሱም በዚያው አቅራቢያ ሰፊ ቦታ እንዲሰጧቸውና የመኖሪያ ቤታቸውንም እንዲሰሩ ጠየቋቸው ንጉሱም ለንግስቲቱ በሰጧቸው ቦታ ላይ ንግስቲቱ በዘመኑ ውብ የሆነ መኖሪያቸውን ሊሰሩ ችለዋል፡፡
ከአንድ አመት በኋላ በ1987 ዓም ንግስት ጣይቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የእንጦጦ መኖሪያቸውን በመልቀቅ መኖሪያቸውን በፍል ውሃ አካባቢ መሰረቱ ፡፡ መኳንንቱና መሳፍንቱ ከንጉሱ በተሰጣቸው ቦታ የየራሳቸውን መኖሪያ ቤበቶች በመመስረት ከተማዋ እንደከተማነት እንድትጠናከር የራሳቸውን እገዛ አድርገዋል፡፡
በሚያዚያ 1891 ዓም ከሁለት ዓመት በኋላ አፄ ምኒሊክ ለከተማዋ የመጀመሪያ የድንጋይ ቤት የሆነውን ስላሴ ቤ/ክ አስገነቡ ይህንንም ተከትሎ ከተማዋን እንዲያለሙ ንጉሱ ለጥቂት የአውሮፓ ዜጎችና ለመሳፍንቱ በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች ለህንፃ ለቤት መስሪያ የሚሆኑ ቦታዎችን ማከፋፈል ጀመሩ ፡፡ከዚህም ጎን ለጎን ንጉሱ ለመኳንንቱና መሳፍንቱ የሚሆን የርስት መሬት ከከተማ ወጣ በማለት እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡
መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ
የአገሪቱ ታላቅ ከተማና የፌዴራል መንግስት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ ከምድር ወገብ በስተሰሜን በ90 ላይ ትገኛለች፡፡ከተማዋ በአቀማመጧ በመሃል ላይ ትገኛለች፡፡የከተማዋ ከፍተኛ ቦታ እንጦጦ ሲሆን ከፍታውም ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር ነው፡፡የከተማዋ ዝቅተኛ ቦታ አቃቂ ሲሆን ከባህር ጠለል በላይ 2100 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ከተማዋ በአለም ላይ በከፍተኛ ስፍራ ከሚገኙት ከተሞች ከላፓዛና ከኩዩት በመቀጠል በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡አዲስ አበባ በአየር ንብረቷ ምቹ ከመሆኗም በላይ ዙሪያዋን በዝቋላ፣በኤረር፣ በፍሪና፣በወጨጫ እና በመናገሻ ከተሞች የተከበበች ናት፡፡
ከተማዋ ከተቆረቆረችበት ዕለት አንስቶ በአስደናቂ ሁኔታ ትገኛለች ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የከተማዋ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 540 ስኩዌር ኪ.ሜ ነው፡፡የከተማዋን ህዝብ ቁጥር በተመለከተ ከተማዋ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ይገኙባታል፡፡ከተማዋ የተለያዩ አለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች መቀመጫ ፣ከአንድ መቶ በላይ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች መቀመጫ ናት፡፡በዚህም ከዋሽንግተን ፣ኒውዮርክና ለንደን ቀጥሎ ኢምባሲዎችና አለምአቀፍ ድርጅቶች የሚገኙባት ከተማ ናት፡፡
የአየር ንብረት
ምንም እንኳን ለምድር ወገብ ቅርብ ብትሆንም የከተማዋ በከፍተኛ ቦታ ላይ መገኘት አዲስ አበባ ምቹና ተስማሚ የአየር ንብረት እንዲኖራት አድርጓታል፡፡ዓመቱ የከተማ የአየር ንብረት ያን ያህል የጎላ ለውጥ የለውም፡፡ ሆኖም ግን ከሰኔ እስከ መስከረም አጋማሽ ያለው ወቅት ዝናባማ ወቅት ሲሆን በዚህን ጊዜ የአየር ንብረቱ ከወትርው ቀዝቀዝ ያለ ነው፡፡ የከተማዋ አመታዊ አማካይ ዝናብ መጠን 1160 ሚሊ ሜትር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 80 የሚሆነው ከሰኔ እስከ መስከረም ወራት የሚዘንበው ዝናብ ነው፡፡ በአንጻሩ ሚያዚያና ግንቦት ደረቃማ ወራት ሲሆኑ በመጋቢትና በሚያዚያ መግቢያ ላይ ጥቂት የበልግ ዝናብ አለ፡፡







ታሪክ





