Partly Cloudy Partly Cloudy Sunny
21C 26C 25C
ክስኞ ሮብ
ሙዝየም

ሙዝየም

በኢትዮጵያ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶችን የመጠበቅና የመንከባከብ እንቅስቃሴ የተጀመረው ኢትዮጵያዊያን ሣይንቲስቶች ከፈረንሣይ አቻዎቻቸው ጋር የአርኪዎሎጂ ጥናት ማድረግ በጀመሩበት ወቅት ነበር፡፡ በወቅቱ በአርኪኦሎጂ ዙሪያ የተደጉት ጥልቅ ጥናቶች ከጥናቱ የሚኙትን የአርኪኦሎጂ ውጤቶችን በሙዚየም ለማከማቸትና ለእይታ ለማቅረብ ሙዚየሙን መገንባት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመበት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በ1944 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡ ሙዚየሙ ሲመሰረት ጥቂት ቅሪቶችን በማሰባሰብና ስለአገሪቱ ብሔረሰቦች ክብረ በዓላት የሚያንፀባርቁ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ ነበር፡፡ ሙዚየሙ በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ እያደገ ሄደ፡፡ በዚህ ሂደትም ውስጥ ሙዚየሙ አሁን ያለበትን ሕንፃ ለመገንባት በቅቷል፡፡

ሙዚየሙ በአራት ክፍሎች የተከፋፈለ ነው፡-
  • የመጀመሪያው ክፍል ስለሰው ልጅ አመጣጥ ቅድመ ታሪክ የሚያሣይ ሲሆን በዚህ ክፍል የሉሲ አጽምና ቀደምት የሰው ልጆች የሚጠቀሙባቸው የድንጋይ መሣሪያዎችን ይዟል፡፡
  • በሁለተኛው ክፍል ታሪካዊና አርኪኦሎጂካዊ ግኝቶች የሚገኙበት ሲሆን በዚህ ክፍል ከአክሱም በፊት እስከ 16 ክ/ዘመን ያለውን ገጽታ ያሣያል፡፡
  • በሶስተኛው ክፍል የብሔር ብሔረስቦችን ባህልና የክብረ በዓላት ሥርዓት፣ ጊጣጌጦች የሚንፀባረቁበትና የብሔር ብሔረሰቦች ባህል የሚታይበት ነው፡፡
  • በአራተኛው ክፍል ዘመናዊ የሥነ ስዕል ጥበብ ሲገኝ በሥሩም በተለያዩ ኢትዮጵያውያን የተሣሉና የተቀረፁ ሥዕልና ቅርሳ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡

ሙዚየሙ ለጐብኚዎች ምቹ ነው፡፡ ምክንያቱም በእያንዳንዱ ቅርስ /እቃ ላይ ስለእቃው ዝርዝር መረጃ ይገኛል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሙዚየሙ ከመደበኛው ሥራው በተጨማሪ ሙዚየሙን ለመጐብኘት ለሚፈልጉ ተማሪዎችና ጐብኚዎች ልዩ የጉብኝት ፕሮግራም ያዘጋጃል፡፡ ሌላው በሙዚየሙ የሚሰጠው አገልግሎት ቱሪስቶች የሚገዟቸውን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ውጪ እንዳይወጣ ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ በቅርሶች ላይ ፍተሻ ያደርጋል፡፡

አድራሻ፡- አምስት ኪሎከብሉቶፕ ሬስቶራንት ፊት ለፊት
ስ.ቁ፡- +251.11 111 9131/ ext 715ዐ
የጉብኝት ሰዓት፡- ከሰኞ - እሁድ /ከሕዝብ በዓላት በስተቀር/ ከ2፡3ዐ - 11፡3ዐ ሰዓት

ከባህር ጠለል በላይ 3ዐዐዐ ሺ ሜትር ላይ በሚገኘው የእንጦጦ ተራራ ዳግማዊ ምኒልክ አዲስ አበባን መስረተዋል፡፡ በዚህ ሥፍራ የንጉሱ ቤተመንግሥት ይገኛል፡፡ ይህ ቤተመንግሥት ከተማዋን ታኮ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ ለጐብኚዎች አመቺ የሆነ የትራንስፖርት መንገድ አለው፡፡ በትራንስፖርት መጠቀም ያልፈለጉ ጐብኚዎች መንገዱ አመቺ በመሆኑ ወደሥፍራው በእግራቸው በቀላሉ መድረስ ይችላሉ፡፡ ወደሥፍራውም ሲደርሱ በአካባቢው በሚገኙ ዛፎችና አበቦች ውበትና በአካባቢው ያለው ነፋሻ አየር ይደሰታሉ፡፡ ከዚህም አልፎ የእንጦጦ ሙዚየምና በውስጡ የሚገኙ ደረጃቸውን የጠበቁና ታሪካዊ ይዘት ያላቸውን ውድ ቅርሶች ይጐበኛሉ፡፡ በሙዚየሙ ውስጥ ከሚገኙ ታሪካዊ ክርሶች ወደ አድዋ ጦርነት ክተት ሲታወጅ ሲጐሰም የነበረው ነጋሪት፣ አፄ ምኒልክ አንኮበር በነበሩበት ወቅት ሲጠቀሙበት የነበረው አልጋ፣ የአፄ ምኒልክ ዘውድ፣ አፄ ምኒልክ የሚጠቀሙበት የፔርሺያን ምንጣፍ ይገኛሉ፡፡ ከሙዚየሙ አንፃር ዓይንን የሚስበው በአፄ ምኒልክ የተገነቡት የቅዱስ ራጉኤልና የቅድስት ማርያም አብያተ ክርስቲያናት፣ የአፄ ምኒልክ የቀድሞ ቤተመንግሥት ፀለሎች ሊጐበኙ የሚባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

አድራሻ፡ በእንጦጦ ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ
ስ.ቁ፡ +251.11 666 ዐ465/6/7

የባህልና የቱሪዝም ሀብቶቻችን
በከተማችን ልማት ውስጥ
ግንባር ቀደም ተዋናዮች እንዲሆኑ
እንሰራለን፡፡

         
Developed by JoomVision.com

መረጃዎች እንድንልክልዎ ይመዝገቡ