Partly Cloudy Partly Cloudy Sunny
21C 26C 25C
ክስኞ ሮብ

ጥናትና ምርምር

የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም በ1963 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡ ምርምር ተቋሙ ሲቋቋም ሶስት ዓላማዎችን ለማሳካት ታስቦ ነው፡፡ እነዚህም ምርምርና ሥርፀትን ለማከናወን፣ የህትመት ማዕከል ለመሆንና የአገሪቱን ቋንቋ ባህልና ታሪክ ለቀሪው ዓለም ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የቀደምትነት ሥልጣኔና የሰው ልጅ መገኛ እንደመሆኗ መጠን ሙዚየሙ የብሔር ብሔረሰቦችን ቱባ ባህል በውስጡ ይዞ ይገኛል፡፡ ከሁሉም በላይ ሙዚየሙ ጥንታዊ ቅርሶችን የያዙ ሲሆን ይህንንም በዘላቂነት ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ትልቅ ራዕይን አንግቧል፡፡

ከላይ እንደተገለፀው የኢትኖግራፊክ ሙዚየም በአገሪቱ ያሉ የተለያዩ ብሔርና ብሔረሰቦች ባህልን በአንድ ጣራ ሥር አካቶ የያዘ ተቋም ነው፡፡ ሙዚየሙ በመግቢያው ላይ በአገሪቱ የሚኙ ብሔር ብሔረሰቦች ህይወትን ከውልድት እስከሞት አልፎም ከሞት ወዲያ እንዴት እንደሚመከቱት ያሣያል፡፡ የመጀመሪያው ፎቅ ላይ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴን አልጋንና የኢትኖግራፊክን ክፍል ሲያኙ በሁለተኛው ፎቅ ላይ የአገሪቱን የእደ ጥበብ ውጤቶች ያገኛሉ፡፡ በመጀመሪያ ፎቅ ላይ የሚገኘውንና ንጉሡ ለ1ዐ ዓመታት የተገለገሉበትን አልጋ በተመለከተ አልጋው በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ ያለችበትን የሥልጣኔ ደረጃ የአገሪቱ ቤተመንግሥት በወቅቱ በአውሮፓ ከነበሩት ቤተመንግሥታት ጋር ተመሳሳይ ይዘት እንዳለው ያሣያል፡፡ ወደኢትኖግራፊክ ክፍል ሲያመሩ በአገሪቱ የሚኙ ከ8ዐ የሚበልጡ ብሔር ብሔረሰቦች የሚገለገሉባቸውን እቃዎች ያኛሉ፡፡ ይህ ክፍል በሁለት ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያው የአገሪቱን የሶሻልና ኢኮኖሚ አጠቃላይ ገጽታ የሚያሣይ በተጨማሪም የብሔር ብሔረሰቦች የማምረቻ መሣሪያዎችና የእደ ጥበብ ቴክኒኮችን ያሣያል፡፡ የሁለተኛው ክፍል ኢትዮጵያን በአጭሩ ያሳይዎታል፡፡ በዚህ ክፍል ከአገሪቱ ክልሎች የተሰባሰቡ የተለያዩ እቃዎችን ያገኛሉ፡፡

በሙዚየሙ በሚኘው ሁለተኛ ፎቅ ላይ የአገሪቱ የሥነ ሥዕል ጥበብ ይመለከታሉ፡፡ በዚህ ክፍል የኢትዮጵያን መንፈሣዊና አለማዊ ገጽታን በሥነ ሥዕል ጥበብ እንመለከታለን፡፡ በዚህ ክፍል በ14ኛው ክፍለ ዘመን ላይ የተሣሉ አንዳንድ ስዕሎችን እናገኛለን፡፡

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ቅጥር ግቢ
ስ.ቁ፡- +251.11 123 9739/ ext 715ዐ
የጉብኝት ሰዓት፡- /ከበዓላት በስተቀር/ ከሰኞ - አርብ ከ2፡0ዐ - 11፡0ዐ ሰዓት
ቅዳሜና እሁድ ከ3፡ዐዐ - 11፡ዐዐ ሰዓት

የባህልና የቱሪዝም ሀብቶቻችን
በከተማችን ልማት ውስጥ
ግንባር ቀደም ተዋናዮች እንዲሆኑ
እንሰራለን፡፡

         
Developed by JoomVision.com

መረጃዎች እንድንልክልዎ ይመዝገቡ