Partly Cloudy Partly Cloudy Sunny
22C 26C 25C
Monday Tuesday Wednesday

የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ6 ወራት የእቅድ ክንውን የከተማዋን መልካም ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደነበረው ተገለጸ፡፡ Featured

የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ6 ወራት የእቅድ ክንውን የከተማዋን መልካም ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደነበረው ተገለጸ፡፡ 

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ.ም በቢሮው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የ6 ወር የእቅድ አፈፃፀም ውይይት ሲካሔድ የቢሮው ኃላፊ አቶ ገ/ፃዲቅ ሀጎስ የመሩት ሲሆን በስሩ ያሉ ተቋማት እና የ10 ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ስራ ሂደቶች ተገኝተዋል፡፡
በቢሮው የጥናት እቅድና በጀት ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል አሰፋ የነበረውን ክንውን ሲያብራሩ ባሳለፍነው 6 ወራት ውስጥ ልማታዊ ባህልን የሚያጎለብቱ እና የቱሪዝም ልማቱን የሚያፋጥኑ በርካታ ቁልፍ ተግባራት መከናወናቸውን ፣ የዘመን መለወጫ የሙዚቃ ዝግጅት በቴአትር ቤቶች ልዩ ልዩ መልእክት ያላቸው ሙዚቃዎች ፣ ድራማዎች ፣ የፓፔት ትርኢቶች  የህጻናትና አዋቂ ቴአትሮች በመድረክ ለህዝብ እንደቀረቡ ፣ በባህልና ቱሪዝም ልማት ላይ የሚያተኩሩ 26 የሬዲዮ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው መተላለፋቸውን ፣ 29 ሺ 30 መጽሄቶች ፣ ብሮሸሮች ፣ የመልካም ዘመን ምኞት መግለጫ ካርዶች መሰራጨታቸውን ፣ 2 የዶክመንተሪ ፊልሞች የከተማዋን መልካም ገጽታ ግንባታና የቱሪስት ፍሰት እንቅስቃሴው ዓይነት መጨመሩ አላማቸው አድርገው እና የአዲስ አበባን 125ኛ ዓመት የልደት በአል አስመልክቶ የከተማዋን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚያስገነዝቡ ዶክመንተሪ ፊልም ተዘጋጅተው ለህዝብ ተሰራጭተዋል፡፡ ለ1 ሺ 276 የባህል እና ቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በህግ እና ደንቡ መሰረት እየሰሩ ሰለመሆኑ ክትትል ተድርጎ 1ሺ 85ቱ በተሰጣቸው ድጋፍ በአሰራራቸው ላይ ማሻሻያ ማድረጋቸውን በተጨማሪም ለ494 ክበባትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቴክኒክ ድጋፍ መደረጉ ፣ የአዲስ አበባ ሙዚየም ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ በመጡ 2 ሺ 875 ሰዎች መጎብኘቱን ፣ የንባብ ባህልን ለማዳበር በመሰራቱ ለ371 ሺ 126 ሰዎች መጽሀፍት ውሰት እና የንባብ አገልግሎት መሰጠቱን ፣ በተለያዩ ህዝባዊ ባዓላት ከማእከል እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ ባለው መዋቅራችን 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን ማሳተፍ 

መቻሉን ለ180 ሺ 415 የከተማዋ ህብረተሰብ ክፍሎች መረጃ እንዲያገኙ መደረጉን ፣ በህገወጥ ቅጂ መብት ጥሰት ላይ በክፍለ ከተሞች አበረታች ክንውኖች የነበሩ መሆኑን እና 8 ጥናቶችን 
ተካሄደው አብዛኞቹ በመድረክ ለህዝብ መቅረባቸውን ፣ ከቴአትር ቤቶች እና ከአዲስ አበባ ሙዚየም የውስጥ ገቢ ብር ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አንድ ሺ አንድ መቶ አስራ አራት ብር ከአስራ ሁለት ሳንቲም      /2.341.114.12/ ከነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ብር ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ሺ ሶስት መቶ ሰላሳ አምስት ብር /291,335/ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱም ተሳታፊዎች ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል የሆቴሎች የደረጃ ምደባ እና ፈቃድ አሰጣጥ ፣ የለውጥ ስራዎች /BPR እና BSC/ ተፈጻሚነት ፣ የሰው ኃይል እጥረት ፣ የተሞክሮ ልውውጥ እና የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት እንደሚገባ ጠቅሰው በጥቅሉ ቢሮው አሁን ያለው አፈጻጸም አበረታች ቢሆንም ባለፈው አፈጻጸም ያጋጠሙ ማነቆዎችንና ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ ከስር ከስር መፍትሔ እየተበጀላቸው በቅንጅት ከተሰራ የመዲናችን አዲስ አበባ መልካም ገጽታ የመገንባት ስራው ከመቼውም ጊዜ የተሸለ ማድረግ እንደሚቻል ከመግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

የባህልና የቱሪዝም ሀብቶቻችን
በከተማችን ልማት ውስጥ
ግንባር ቀደም ተዋናዮች እንዲሆኑ
እንሰራለን፡፡

         

Subscribe to our newsletter

Find in Addis - Map